የአባላት ንቅናቄ መድረክ እና የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ!

​ፎርቹን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ሥራ ማህበር ኮር አባላት ለታማኝነታቸውና ለላቀ ተሳትፏቸው” እውቅና የተሰጠበት እና የቀጣይ ጉዞ ስትራቴጂዎች ላይ ውይይት የተደረገበት ፣ ደማቅ የአባላት የንቅናቄ መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

ማህበሩ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በአስደናቂ ቁርጠኝነት፣ በታማኝነት እና በላቀ ተሳትፎ ተቋሙን ዛሬ ለደረሰበት  ደረጃ ላበቁት የኮር (Core) አባላት የዕውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል።

ይህ የዕውቅና ሥነ-ሥርዓት ማህበሩ ለአባላቱ ያለውን ከፍተኛ ክብርና ዋጋ የመስጠት ባህል ማሳያ ከመሆኑም በላይ፣ በቀጣይም ሌሎች አባላት ይበልጥ እንዲሳተፉ የሚያበረታታ ሆኖ አልፏል።

በመድረኩ ላይ የማህበሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የቦርድ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ በማህበሩ የቀጣይ ጉዞ፣ አዳዲስ የቁጠባና የብድር አገልግሎቶች እንዲሁም የአባላትን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል በሚቻልባቸው ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

​የማህበሩ አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክት፥ ፎርቹን  በቀጣይም የአባላቱን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማሳደግ፣ ዘመናዊ አሰራሮችን ለመዘርጋት እና አስተማማኝ የፋይናንስ አጋር ሆኖ ለመቀጠል በሙሉ ቁርጠኝነት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

​ለተቋማችን ዕድገት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ ውድ የኮር (Core) አባላቶቻችን፣ እንኳን ደስ አላችሁ!

ፎርቹን ኃ/የተወሰነ መ.የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር
📍አድራሻ :- ዋና መ/ቤት ለገሀር አመልድ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
ቅርንጫፍ :ጦር ሃይሎች ሙሉ ወንጌል ጀርባ ማክዳ ህንፃ 5ኛ ፎቅ
  ለበለጠ መረጃ :-
+2519-9 869 0969
+2519-9 860 6626

✈️T

Posted in
Uncategorized

Wondwossen

Post a comment

Your email address will not be published.

Ethiopia’s leading savings and credit cooperative, dedicated to uplifting communities with innovative financial solutions and fostering sustainable development.